About

መቋቋም

መርሲዶ ሁሉአቀፍ የማህበረሰብ ልማት ማህበር (Multi Responsive Community Development Association (MRCDO) የተባለ ማህበር በነሐሴ 16/ 2016 ዓ.ም ተቋቁሟል፡፡

ስያሜ

በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የተቋቋመው መርሲዶ ሁሉአቀፍ የማህበረሰብ ልማት ማህበር (Multi Responsive Community Development Association (MRCDO) ማህበር በሚል ስም የሚጠራ ሲሆን ከዚህ በኋላ “የበጎ አድራጐት ድርጅት” ተብሎ ይጠቀሳል፡፡

የበጎ አድራጎት ማህበሩ ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው

  1. የማህበረሰቡን የሠላምና የማህበራዊ ትስስር እሴቶች በሚያስጠብቁ ተግባራት ላይ ለመስራት
  2. ወጣቶች፣ ሴቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በልዩ ልዩ የሥራ ማስገኛ ተግባራት እንዲሳተፉ የሚያስችሉ ግብዓቶችንና ሥልጠናዎችን ከአጋር አካላት ጋር በመሆን ለመስጠት
  3. በፌድራልም ሆነ በክልል ደረጃ የማህበረሰቡን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊ ተሳትፏቸውን የሚመለከቱ መመሪያዎች፣ ደንቦች፣ ህጎች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ሲወጡ የትኛውንም የማህበረሰብ ክፍል የሚጠቅሙ እንዲሆኑ የአድቪኬሲ ሥራ ለመስራት
  4. አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንና አነስተኛ ነዋሪ የህብረተሰብ ክፍሎች ጊዚያዊና ቋሚ ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት
  5. የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ሥልጠናዎችንና ግብዓቶችን ለመምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች ለመስጠት የሚያስችሉ ሥራዎችን ከአጋር አካላት ጋር ለመስራት
  6. በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ነገር ግን የተሻለ የትምህርት አቀባበል ያላቸውን ሕፃናትና ወጣቶች የነፃ ትምህርት እድል፣ የቱቶሪያል ክፍያ፣ የቤት ኪራይ፣ የትምህርት ቁሳቁስ ወጭና የገንዘብ ድጋፍ፣ የንፅህና መጠበቂያ መሣሪያዎች ወዘተ. የሚያገኙበትን ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ ይሠራል
  7. የማህበረሰቡን ጤናና ንፅህና ለመጠበቅ የሚያስችሉ ግብዓቶችንና ስልጠናዎችን ለመስጠት
  8. የወጣቶችና ሴቶችን ህገወጥ ስደትን፣ የሴተኛና ጎዳና ተዳዳሪነትን እንዲሁም ልመናን ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ይሰራል
  9.  በሠላምና ግጭት ጥናት ዙሪያ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶችና ተቋማት የምርምርና የማማከር አገልግሎት ይሠጣል
  10. ወጣቶች ስለሀገራቸው በቂ መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል የመረጃ አገልግሎት ማዕከል ይዘረጋል
  11.  ማህበረሰብን የተመለከቱ ጥናታዊ ፅሁፎችን፣ ፎረሞችን፣ ልዩ ዝግጅቶችንና ኤግዚቢሽኖችን የማቅረብና የማዘጋጀት ሥራ ይሰራል
  12. የበጎ አድራጎት ድርጅቱ አባላትና ሠራተኞች በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የልምድ ልውውጥና ሥልጠናዎችን የሚያገኙበትን መንገድ ያመቻቻል